ቀዳሚ ገጽ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን።

ነስሑ እስመ ቀርበት መንግሥተ ሰማያት ማቴ. ፫፥፪፣ ማር. ፩፥፪፣ ሉቃ. ፫፥፫

መንግሥተ ሰማያት በልጅነት፤ ልጅነት በሃይማኖት ልትሰጥ ቀርባለችና እመኑ፤ ንስሐ ግቡ

ውድ አንባቢያን በቅድሚያ በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስዮሐንስ ስም በአሜሪካ ሀገር የመጀመሪያ ወደ ሆነው ወደ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተ ክርስቲያን ድረ ገጽ እንኳን ደህና መጡ። አገልግሎቱን በእውን ለማየትና ለመገልገል የቻልነውንም እንኳን ለዚህ አበቃን እላለሁ።

ሙሉውን ያንብቡ

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅዱስ ገብርኤልና አባቱ ዘካርያስ ትንቢት የተናገሩለት፤ ከሕፃንነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን ያገለገለ፤ በፍጹም ልቡ ዓለምን የናቀ፤ ከተድላዋና ከደስታዋም የተለየ፤ አምላክን ለማጥመቅ የታደለ ሐዋርያ፣ መምህር፣ ሰማዕት፣ ባሕታዊ፣ ነቢይ፣ ጻድቅ ነው፡፡

ሊቁም ከመላእክት፣ ከነቢያት፣ ከካህናት፣ ከሐዋርያት መካከል እንደርሱ መለኮትን ለማጥመቅ የተመረጠ አለመኖሩን በመጥቀስ ‹‹… ዮሐንስ ከማከ ሶበ ፈተዉ ወጽሕቁ፤ እሳተነዳዴ ኢተክህሎሙ ያጥምቁ፤ ራጉኤል በትጋሁ ወኢዮብ በጽድቁ፤ … ዮሐንስ ሆይ! ራጉኤል በትጋቱ፣ ኢዮብምበጽድቁ ቢመኙም ኾነ ቢጨነቁ እንደ አንተ የሚነድ እሳትን (መለኮትን) ሊያጠምቁ አልተቻላቸውም›› ሲል ታላቅነቱን መስክሮለታል (መልክአ ዮሐንስ መጥምቅ፣ ለአዕይንቲከ)፡፡

ዮሐንስ ማለት ‹‹እግዚአብሔር ጸጋ ነው›› ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ወንጌልም መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን ፍሥሐ ወሐሴት (ተድላና ደስታ) ይለዋል፤ ወላጆቹ በእርሱ መወለድ ተደስተዋልና (ሉቃ. ፩፥፲፬)፡፡ በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ አንድ፣ ከቍጥር አንድ ጀምሮ እንደ ተገለጸው ካህኑ ዘካርያስ እና ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ዅሉ በመፈጸም ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ፡፡ ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም፡፡ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድም እግዚአብሔርን ዘወትር ይማጸኑት ነበር፡፡

Continue reading “መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ”

ትምህርት

  • ቅበላ የኅሊና ዝግጅት ወይስ?
    ይህንን ጽሑፍ በ2007ዓ.ም በwww.eotcmk.org ለንባብ ያበቃሁት ሲሆን ዛሬም ሰሞነኛ ሆኖ መጥቷልና መልካም ንባብ። ቅበላ ማለት የጾም ዋዜማ ፣ጾም ከመግባቱ በፊት ቀደም ብሎ ያለው ቀን ወይም ሰሞን ማለት ነው፡፡ በአትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓትና ትውፊት መሠረት ሰንበታት፣ አጽዋማትና በዓላት በዋዜማው በጸሎት (በምኅላ)፣በመዝሙር፣በትምህርት ወዘተ. ልዩ አቀባበል ይደረግላቸዋል ፡፡ ለምሳሌ አይሁድ ሰንበትን(ቅዳሜ) ሲያከብሩ በዋዜማው አቀባበል ያደርጉላታል፡፡ ዓርብ ፀሐይ ሲገባ …
  • የጥምቀት ከተራ በዓል አከባበር የትመጣ
    ይህን ጽሑፍ ጥር 9 ቀን 2006 ዓ.ም በማኅበረቅዱሳን ድረ-ገጽ/ www.eotcmk.org አውጥቼው የነበረ ሲሆን አሁን መጠነኛ ማስተካከያ ተደርጎበታል፡፡ ከተራ ከበበ ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡ የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥል ይውላል፡፡ …
  • ጥምቀት
    ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† <<< በዓለ ኤጲፋንያ >>> ††† “ኤጲፋንያ” የሚለው ቃል ከግሪክ (ጽርዕ) ልሳን የተወሰደ ሲሆን በቁሙ “አስተርእዮ: መገለጥ” ተብሎ ይተረጐማል። በነገረ ድኅነት ምሥጢር ግን ኤጲፋንያ ማለት “የማይታይ መለኮት የታየበት: እሳተ መለኮት በተዋሐደው ሥጋ የተገለጠበት” እንደ ማለት ነው። “ዘኢያስተርኢ ኅቡዕ እስመ አስተርአየ ለነ። እሳት በላዒ አምላክነ።” እንዲል። (አርኬ) …

ስለእኛ

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በሰሜን አሜሪካ በድሲ አና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

መልአከ ጽዮን ቀሲስ በላቸው ወርቁ የደብሩ አስተዳዳሪ

የሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያነሳሳቸው ካህናት፣ ምዕመናንና ምዕመናት ተሰባስበው ሲመካከሩ ከቆዩ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ለመትከል በመወሰናቸው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በዚያን ጊዜ የዲሲና ካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፈቃድ በ፳፻፱ ዓ.ም (2017 እ.አ.ዘ) የተተከለ ነው። ቤተ ክርስቲያኑ የተተከለው በሜሪላንድ ግዛት በሞንትጎሞሪ ክልል ማለትም በራክቪል፣ ጌተርስበርግ፣ ኦልኒ፣ ጀርመን ታውን፣ ክላርክስበርግ፣ ፖቶማክ፣ ሲልቨርስፕሪንግ፣ ወዘተ. አካባቢ የሚገኙ ምዕመናን በቦታ ርቀት ምክንያት ወደ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ለመሄድ ባለመቻላቸው መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲያገኙና የምሥጢራት ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው።

Continue reading “ስለእኛ”